ግዛው ለገሠ 
ሁነኛውን ማኅበራዊ ውል ፍለጋ [EPUB ebook] 
ዘመናትን የተሻገሩ ፈላስፋዎች እና የፖለቲካ እሳቤዎቻቸው

Ajutor

በዚህ መፅሐፍ ውስጥ የምናገኛቸው ፈላስፎች እና የፖለቲካ እሳቤዎቻቸው ዓለም እዚህ ደረጃ ላይ ለመድረሷ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ናቸው። ለሰው ልጅ የአኗኗር ሁናቴ የተሻለ መንገድ ለማሳየትና ለመቀየስ የጣሩ፣ በጥረታቸውም አያሌ ሕዝቦችን ከጨለማ ያወጡ፣ በእሳቤዎቻቸውም ከግለሰብ ባሻገር የሀገራትን ህልውና ያቀኑ ናቸው።

ምን ዓይነት የህብረተሰብ አደረጃጀት ይበጃል? የመንግሥት መኖር ጥቅም ምንድነው? ይኑር ከተባለስ ምን ዓይነት መንግሥትና የመንግሥት ሥርዓት ይሻላል? የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ባሕሪይስ ለአጠቃላዩ የህብረተሰብ አደረጃጀት ምን ሚና ይጫወታል? የመንግሥትነት ሥልጣን ከእግዚአብሔር የተሰጠ ነውን? ወይንስ በሕዝቦች ስምምነት የተፈጠረ? መንግሥት ጨቋኝ የሚሆነው በተፈጥሮው የተነሳ ነው፣ ወይስ ለጠቅላላው ጥቅም በሚል ግብ? ለአምባገነን የተመቸ ሕዝብ አለን? የግለሰብ መብትስ እስከምን ድረስ ነው? እነዚህን እና ሌሎች መሰል ጥያቄዎችን በማንሳት ትውልዶችን ያነጋገሩ እሳቤዎችን አፍልቀዋል።

ለመጽሐፉ “ሁነኛውን ማኅበራዊ ውል ፍለጋ” የተሰኘ ርዕስ የተሰጠበት ምክንያት፣ አብዛኛዎቹ የፖለቲካ ፍልስፍና እሳቤዎች በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ ለሰው ልጆች የተሻለውን ማኅበራዊ ውል (Social Contract) ከመጠቆም ወይም ይዘቱን እና አተገባበሩን ከማብራራት ጋር ዝምድና ስላላቸው ነው። በርግጥ ከማኅበራዊ ውል ጋር በተያያዘ ብዙውን ጊዜ ስማቸው የሚጠቀሰው እንደ ቶማስ ሆፕስ፣ ጆን ሎክ እና ሩሶ ያሉት ፈላስፎች ናቸው፤ መጽሐፉ የእነሱንም እሳቤዎች አካትቷል። በዚህ መጽሐፍ ውስጥ ከግለሰብ እስከ ቡድን መብት/ኃላፊነት፣ ከጋራ ጥቅም እስከ ማኅበራዊ ውል፣ ከመንግሥት ባሕሪይ እና አስፈላጊነቱ፣ እንዲሁም ለዜጎችም ሆነ ለመንግሥት ሊበጁ እስከሚገቡ ገደቦችና ሌሎች አያሌ የፖለቲካ እና የአስተዳደር እሳቤዎች ተተንትነዋል። ለፖለቲከኞች፣ ለፀሐፍት፣ እንዲሁም ሀገር እና ፖለቲካ ግድ ለሚላቸው ሁሉ – ከላይ ከላይ ሳይሆን ከጽንሰ-ሀሳብ አንስቶ መረዳትን ለሚሹ ሁሉ – ጥሩ ግብዓት እንደሚሆን አምናለሁ። መልካም ንባብ።

€9.52
Metode de plata
Cumpărați această carte electronică și primiți încă 1 GRATUIT!
Format EPUB ● Pagini 200 ● ISBN 6610000719068 ● Mărime fișier 8.4 MB ● Editura PublishDrive ● Publicat 2025 ● Descărcabil 24 luni ● Valută EUR ● ID 10172015 ● Protecție împotriva copiilor fără

Mai multe cărți electronice de la același autor (i) / Editor

44.019 Ebooks din această categorie