Adel Ben-Harhara 
ፍ ለ ጋ [EPUB ebook] 
ያላገኘሁትን ማንነቴን ማደን

Stöd

’ፍለጋ’ የተሰኘው ይህ የባለ ሦስት ቅጽ እኔ በእንተእኔ ሁለተኛ ጥራዝ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የየመን ሙዋላዲኖች (በውጭ ሀገራት ተወላጅ የሆኑ የመኖች) ለእኩል መብትና ለዜግነት ፍቃድ ስለሚያደርጉት ትግል ያወሳል። መሃይምነትና ተከታታይ የጎሳ ግጭቶች ልማትንና ዘመናዊነትን በማጨናገፍ፣ አሁንም ሀገሪቱንና አካባቢዋን በማወክ ላይ ናቸው።

ወደ ቅድመ አያቶቹ ምድር በተሰደደ አንድ የአሥራ ስድስት ዓመት ልጅ ተጋድሎ ውስጥ፣ የየመንን መሠረታዊ መገለጫዎች ፍንትው አድርገው ለመረዳት ይገድዎታል? እንግዲያውስ ይህ የእርስዎ መጽሐፍ ነው።

በምድር ላይ ካሉት ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዱ የነበረውና፣ የአረብ ሥልጣኔ መገኛ የሆነው፣ የንጉስ ሰሎሞን እንግዳ በነበረችው በመጽሐፍ ቅዱሳዊቷ በንግሥተ ሳባ ምድር መጻተኛው ምን ገጠመው? በሰሜን በኩል ከሴማዊ አገሮችና ከቀይ ባህር ማዶ ከአፍሪካ ቀንድ ባህሎች ጋር ግንኙነት ያላት የመን፣ አሁን በጊዜ ተለዋዋጭነት ተክዳ የመካከለኛውን ዘመን ባህሎች የሙጥኝ ብላለች፡፡

ዓድል በየመን በቆየባቸው ጥቂት ዓመታት መገለልን፣ መድሎንና የእርስ በርስ ጦርነትን ገፈት ቀምሷል፡፡ የሚኮራበት ጠይም የምሥራቅ አፍሪካ የቆዳ ቀለሙ ኋላቀርና ጥንታዊ ከሆነው የየመን ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ እንዳይዋሃድ እንቅፋት ሆኖበት ነበር። ዓድል ይህንን ሁሉ መሰናክል አልፎና የአያት ቅድመ አያቱን ምድር ለቆ፣ ወደ ተሻለ ሀገር መሄድ የቻለው ጠንካራ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ አማራጭ ስለሌለውም ጭምር ነበር።

€18.99
Betalningsmetoder
Köp den här e-boken och få 1 till GRATIS!
Formatera EPUB ● Sidor 145 ● ISBN 9781778023354 ● Filstorlek 0.8 MB ● Utgivare Adel Ben-Harhara ● Publicerad 2024 ● Utgåva 1 ● Nedladdningsbara 24 månader ● Valuta EUR ● ID 9347899 ● Kopieringsskydd Adobe DRM
Kräver en DRM-kapabel e-läsare

Fler e-böcker från samma författare (r) / Redaktör

50 169 E-böcker i denna kategori