Adel Ben-Harhara 
ፍ ለ ጋ [EPUB ebook] 
ያላገኘሁትን ማንነቴን ማደን

支持

‘ፍለጋ’ የተሰኘው ይህ የባለ ሦስት ቅጽ እኔ በእንተእኔ ሁለተኛ ጥራዝ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የየመን ሙዋላዲኖች (በውጭ ሀገራት ተወላጅ የሆኑ የመኖች) ለእኩል መብትና ለዜግነት ፍቃድ ስለሚያደርጉት ትግል ያወሳል። መሃይምነትና ተከታታይ የጎሳ ግጭቶች ልማትንና ዘመናዊነትን በማጨናገፍ፣ አሁንም ሀገሪቱንና አካባቢዋን በማወክ ላይ ናቸው።

ወደ ቅድመ አያቶቹ ምድር በተሰደደ አንድ የአሥራ ስድስት ዓመት ልጅ ተጋድሎ ውስጥ፣ የየመንን መሠረታዊ መገለጫዎች ፍንትው አድርገው ለመረዳት ይገድዎታል? እንግዲያውስ ይህ የእርስዎ መጽሐፍ ነው።

በምድር ላይ ካሉት ጥንታዊ ሥልጣኔዎች አንዱ የነበረውና፣ የአረብ ሥልጣኔ መገኛ የሆነው፣ የንጉስ ሰሎሞን እንግዳ በነበረችው በመጽሐፍ ቅዱሳዊቷ በንግሥተ ሳባ ምድር መጻተኛው ምን ገጠመው? በሰሜን በኩል ከሴማዊ አገሮችና ከቀይ ባህር ማዶ ከአፍሪካ ቀንድ ባህሎች ጋር ግንኙነት ያላት የመን፣ አሁን በጊዜ ተለዋዋጭነት ተክዳ የመካከለኛውን ዘመን ባህሎች የሙጥኝ ብላለች፡፡

ዓድል በየመን በቆየባቸው ጥቂት ዓመታት መገለልን፣ መድሎንና የእርስ በርስ ጦርነትን ገፈት ቀምሷል፡፡ የሚኮራበት ጠይም የምሥራቅ አፍሪካ የቆዳ ቀለሙ ኋላቀርና ጥንታዊ ከሆነው የየመን ማህበረሰብ ጋር በቀላሉ እንዳይዋሃድ እንቅፋት ሆኖበት ነበር። ዓድል ይህንን ሁሉ መሰናክል አልፎና የአያት ቅድመ አያቱን ምድር ለቆ፣ ወደ ተሻለ ሀገር መሄድ የቻለው ጠንካራ ስለሆነ ብቻ ሳይሆን፣ አማራጭ ስለሌለውም ጭምር ነበር።

€18.99
支付方式
购买此电子书可免费获赠一本!
格式 EPUB ● 网页 145 ● ISBN 9781778023354 ● 文件大小 0.8 MB ● 出版者 Adel Ben-Harhara ● 发布时间 2024 ● 版 1 ● 下载 24 个月 ● 货币 EUR ● ID 9347899 ● 复制保护 Adobe DRM
需要具备DRM功能的电子书阅读器

来自同一作者的更多电子书 / 编辑

50,169 此类电子书